በባሌ ዞን አልቪማ ፓስታና የምግብ ኮምፕሌክስ ፋብሪካ ከዩኒየኖችና አርሶ አደሮች ጋር የፓስታ ስንዴ የገበያ ትስስር ስምምነት ተፈራረመ።

በባሌ እና ምስራቅ ባሌ ዞን የሚገኙ አርሶ አደሮች እንዲሁም ዩኒየኖች ለፓስታ የሚሆን ስንዴ በማምረት ለአልቪማ የምግብ ኮምፕሌክስ ፋብሪካ ለማቅረብ ስምምነት ዛሬ በሮቤ ከተማ ተፈራርመዋል።

ከባሌ እና ምስራቅ ባሌ መተው የፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙ አርሶ አደሮች ለኦቢኤን እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም ምርታቸውን በጥሩ ዋጋ ለመሸጥ ሲቸገሩ እንደነበርና አልቪማ ምግብና ፓስታ ኮምፕሌክስ ፋብሪካ የተመረጡ የፓስታ ስንዴ ምርጥ ዘር ሰቶአቸው በባለሙያዎች ድጋፍ ታግዘው በማምረት ለፋብሪካው ለማቅረብ ስምምነት ተፈራርመዋል።

https://youtu.be/pRus0YzsuLo

የምርጥ ዘር እጥረትን ለመፍታትና የተመረጡ የፓስታ ስንዴ ዘሮችን ለአርሶ አደሩ ለማቅረብ የሚያስችል ስምምነት መፈራረማቸውንም የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ የባሌ ቅርንጫፍ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጫላ አበበ ተናግረዋል።

በፊርማው ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት በኦሮሚያ ግብርና ቢሮ የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከል ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ዱፌራ በቀለ እንደተናገሩት ዛሬ የተፈረመው ስምምነት ለአርሶ አደሩ ትልቅ እድል መሆኑን እና ከውጭ የሚገባውን ስንዴ ለማስቀረትም አስተዋፅዖ ይኖረዋል።

አርሶ አደሩ ጥራቱን የጠበቀ የፓስታ ስንዴ በማምረት እንዲያቀርብ አስፈላጊ የሆነ ድጋፍ ይደረጋል ያሉት ደግሞ የባሌ ዞን ግብርና ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ሰለሞን ዳዲ ናቸው ።

የአሊቪማ ምግብና ፓስታ ኮምፕሌክስ ፋብሪካ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወርቅህ ርኪታ በበኩላቸው ከዚህ ቀደም ለፓስታ የሚሆን ዱቄት ከውጭ ሲያስገቡ መቆየታቸውን ተናግረው የፓስታ ስንዴው በ አርሶ አደሮቹ መመረት የውጭ ምንዛሬን ከማስቀረት ባለፈም የተለያዩ ጠቀሜታዎች ይኖሩታልም ብለዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *